ትምህርተ ሂሳብ
From Wikipedia
ትምህርተ ሂሳብ የብዛት፣ የአደረጃጀት የለውጥና የስፋት ጥናት ተብሎ ብዙ ግዜ የታወቃል። ሌሎችም "የቅርጽና የቁጥር" ጥናት ብለው ይጠሩታል። በፎርማሊስቲክ አይን ተጨባጭ ያልሆኑን አደረጃጀቶችን ሥነ አመክንዮንና (ሎጂክ) የሂሳብ አጻጻፎችን በመጠቀም መመርመር ተብሎ ይታወቃል። ሪአሊስቶች ደግሞ ስለነሱ ካለን ግንዛቤ ውጭ ሰለሚኖሩ እቃዮችና ጽንሶች ምርምር ይሉታል። ትምህርተ ሂሳብ በማንኛውም የሳይንስ ዘርፍ ስለሚጠቅም "የሳይስ ቋንቋ" ወይም የጠፈር ቋንቋ ተብሎም ይጠራል።