ቶማስ ጄፈርሰን
From Wikipedia
ቶማስ ጄፈርሰን (ሚያዝያ 7 ቀን 1735 ~ ሰኔ 28 ቀን 1818 ዓ.ም.) ከየካቲት 26 ቀን 1793 እስከ የካቲት 25 ቀን 1801 ዓ.ም. ድረስ የአሜሪካ 3ኛ ፕሬዝዳንት ነበሩ። ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቨርጂኚያን ያቋቋሙት ጄፈርሰንም ነበሩ።
ቶማስ ጄፈርሰን ከአባቱ ከፒተር ጄፈርስን እና ከእናቱ ጄን ራንዶልፍ ተወለዱ። ቶማስ በአሜሪካ አብዮት ጊዜ በ1768 ዓ.ም. ከእንግሊዝ ንጉሥ የአሜሪካ ነጻነት ዐዋጅ ጻፉ። በኋላ ፕሬዚዳንት ሲሆኑ የመርከብ ሃያላት ወደ አልጀርስ ላኩ፣ ከናፖሌዎን ደግሞ ሰፊ መሬት በሚሲሲፒ ወንዝ አቅራቢያ (የሉዊዚያና አቅራቢያ የተባለው) ገዝተው ነበር። ይህ ድርጊት የአሜሪካ ስፋት በሁለት እጅ አስፋፋ።