1768
From Wikipedia
1768 ዓመተ ምኅረት:
- ኅዳር 5 ቀን - የአሜሪካ አብዮታዊ አርበኞች ከፍልሚያ በኋላ ሞንትሬያልን ማረኩ።
- ታኅሣሥ 23 ቀን - የእንግሊዝ ሠራዊት በኬበክ ከተማ አሜሪካውያንን አስመለሳቸው።
- የካቲት 29 ቀን - በሞርዝ ጅረት ድልድይ ፍልሚያ ስሜን ካሮላይና አርበኞች አሸነፉ።
- መጋቢት 10 ቀን - ከአሜሪካውያን መድፍ የተነሣ የእንግሊዝ ሠራዊት ከቦስቶን ይወጣል።
- ሰኔ 3 ቀን - አሜሪካውያን በቷ-ሪቭዬር ፍልሚያ በኬበክ ድል ሆኑ።
- ሰኔ 24 ቀን - ስፓንያውያን ሳን ፍራንሲስኮ ካሊፎርኒያ አቆሙ።
- ሰኔ 29 ቀን - የአሜሪካ ነጻነት ዐዋጅ (ከእንግሊዝ አገር) በቶማስ ጄፈርሰን ተጽፎ በፊላዴልፊያ ታተመ።
- ሐምሌ 4 ቀን - በኒው ዮርክ ከተማ ብዙ ሠልፈኞች ተናድደው የእንግሊዝ ንጉሥ 3ኛ ጆርጅን ሐውልት ያወድቃሉ።
- ሐምሌ 7 ቀን - የእንግሊዝ ዠብደኛ ጄምስ ኩክ በሦስተኛው ጉዞ ወደ ሰላማዊ ውቅያኖስ ከእንግሊዝ ወጣ።
- ነሐሴ 11 ቀን - የጀርመን ቅጥረኛ ወታደሮች የእንግሊዝ ሠራዊት ለመርዳት በኒው ዮርክ ደረሱ።
- ነሐሴ 23 ቀን - የእንግሊዝ ሠራዊት በጆርጅ ዋሽንግተን ላይ በሎንግ አይላንድ ውጊያ አሸነፉ።
- ጳጉሜ 3 ቀን - አንድ አውሎ ንፋስ ጉዋዶሎፕ ሲመታ ከ6000 ሰዎች በላይ ጠፉ።
[ለማስተካከል] እንደ አውሮጵውያን አቆጣጠር
- እስከ ታኅሣሥ 23 ቀን 1768 ድረስ = 1775 እ.ኤ.አ.
- ከታኅሣሥ 24 ቀን 1768 ጀምሮ = 1776 እ.ኤ.አ.