የመርዌ ጽሕፈት
From Wikipedia
维=>ሐ | ይህ መጣጥፍ "የሳምንቱ ትርጉም" ነበር። (የካቲት 27 ቀን 1998 ተመረጠ።) |
የመርዌ ጽሕፈት ከክ.በ. 200 አመት ያሕል ጀምሮ በመርዌ መንግሥት (ዛሬ ሱዳን) የመርዌ ቋንቋ የተጻፈበት ፊደል ነበር። የወጣው ከግብፃዊው ሃይሮግሊፊክና ዴሞቲክ ጽሕፈቶች ነበር። ከመርዌ መንግሥት በኋላ በተከተሉት በኖባ መንግሥታት ደግሞ ክርስትና እስከ ገባ ድረስ ምናልባት ይጠቅም ነበር፡፡ ከክርስትና በኋላ የጥንታዊ ኖባ ቋንቋ የተጻፈበት በግሪክ ፊደል ሲሆን ከዱሮ መርዌ ጽሕፈት 3 ምልክቶች ተጨምረው ነበር፡፡
በጠቅላላ 23 ምልክቶች ነበሩበት፡፡ ከነዚህ መሀል 4 አናባቢዎች፣ እነሱም /አ/, /እ/, /ኢ/, ና /ኦ/ ነበሩ፡፡ የተናባቢ ምልክቶች ለብቻ ሲታዩ የ/አ/ ድምጽ ያሰሙ ነበር፡፡
ለዚህ ፊደል ሁለት አይነቶች እነሱም ሃይሮግሊፊክና ዴሞቲክ ነበሩ፡፡ የሃይሮግሊፊክ ቅርጾች በተለይ የሚገኙ በሐውልቶች ነው፡፡ እሱ ከላይ እስከ ታች ይጻፍ ነበር፣ ዴሞቲክ ከቀኝ እስከ ግራ ይጻፍ ነበር፡፡ ሁለት ወይም ሦስት ነጥብ ቃላት ለመለየት ጠቀመ፡፡
የፊደሎቹ ፍች የገለጸው ሊቅ እንግሊዛዊው ፍራንሲስ ልወልን ግሪፊስ በ1901 ዓ.ም. ነበር፡፡ ዳሩ ግን እስከ ዛሬ ድረስ ቋንቋው እራሱ በደንብ አይታውቅም፡፡