ካሽሚርኛ
From Wikipedia
ካሽሚርኛ (ካሽሚሪ) የህንዳዊ-አውሮፓዊ ቋንቋዎች ቤተሰብ ቋንቋ ሲሆን በተለይ የሚናገርበት በካሽሚር አካባቢ በ 4,611,000 ሰዎች ነው። ካሽሚርም ዛሬ በሕንድ በፓኪስታንና በቻይና የተከፋፈለ አውራጃ ነው።
ይህ ቋንቋ ዛሬ በአብዛኛው የተጻፈ ቋንቋ ሳይሆን የሕዝብ መነጋገርያ ብቻ ነው። ሆኖም ድሮ በሻራዳ ጽሕፈት ከዚያም ላይ በአረብ አልፋቤት የተጻፈ አንዳንድ ጽሑፍ ይኖራል። በታሪክ ከሁሉ አስቀድሞ የተገኘው የካሽሚርኛ ሰነድ የላለሽቫሪ (እሷም ሴት ገጣሚ የሆነች) ግጥሞች ከ14ኛ ምዕተ ዓመት ናቸው።
በፖለቲካ ሳቢያ የማይምነት ጉዳይ በብዛት ቸል ተብሏል። መደበኛ ወይም ይፋዊ ቋንቋ የትም ቦታ እንኳን አይደለም። ባለፉት አስርተ ዓመታቶች በአንዳንድ ከፍተኛ መካነ ጥናት ቋንቋው ቢማርም፣ በልጆች ትምህርት ቤት ደረጃ ግን ገና አይሰማም። እስካሁን በኢንተርኔት ላይ አንድ ጋዜጣ ብቻ በካሽሚርኛ አለ። ይሁንና ጥቂት የካሽሚርኛ መጽሔቶች በመታተም ላይ ይገኛሉ።
[ለማስተካከል] በተጨማሪ ለመረዳት
- ኮሹር የካሽሚርኛ ትምህርቶች (ለእንግሊዝኛ)
- የካሽሚርኛ ትምህርቶች (ለእንግሊዝኛ)
- አንድ የካሽሚርኛ መጽሄት