ነሐሴ 25
From Wikipedia
ነሐሴ 25 ቀን: የነጻነት በዓል በማለይዝያ፤ ትሪኒዳድ፤ ኪርግዝስታን...
[ለማስተካከል] ታሪካዊ ማስታወሻዎች
- 1557 - በዩናይትድ እስቴት ከሁሉ አስቀድሞ በአውሮጳውያን የተሰራ ከተማ ሰይንት ኦገስቲን ፍሎሪዳ ተመሰረተ።
- 1778 - የማሳቹሰትስ ገበሬዎች ቀረጣቸው ከፍተኛ ሆኖ በሸይስ አመጽ ሸፈቱ።
- 1792 - ጌብሪየል ፕሮሰር የባርዮችን ብጥብጥ በሪችሞንድ ቪርጂንያ አሸፈተ።
- 1805 - ክሪክ የተባለው የቀይ ኢንዲያን ጐሣ ወታደሮች በፎርት ሚምስ ምሽግ አላባማ ላይ እልቂት አደረጉ።
- 1805 - የናፖሌዎን ሠራዊት በኩልም ውጊያ ድል ሆነ።
- 1854 - በአሜሪካ መነጣጠል ጦርነት ደቡብ ክፍላገሮች (ኮንፌዴራቶች) በ2ኛ መናሠሥ ውጊያ አሸነፉ።
- 1984 - ፓስካል ሊሱባ በኮንጎ ሪፑብሊክ ምርጫ ፕሬዚዳን ሆኑ፤ ይህ ምርጫ የረጅም ዘመን አንድ ፓርቲ ግዛት ጨረሰ።
- 1989 - ዲያና ፕሪንሰስ ኦፍ ዌልስ በመኪና አደጋ ፓሪስ አረፉ።
- 1990 - ስሜን ኮሪያ የራሱን ሰው ሠራሽ መንኮራኩር መጀመርያ ጊዜ ላከ።
- 1991 - በመስኮብ ሩሲያ የአፓርትማ ሕንጻ መፈንዳት በቸቸን ታጣቂዎች ጀመረ።