User:Elfalem/ድህረ ገጽ
From Wikipedia
ድህረ ገጽ በድኅረ ገጽ መረብ የሚገኝ ፋይል ነው። ይህ ድህረ-ገጽ በተለያዩ የኮምፒውተር ቋንቋዎች መጻፍ ሲችል ኤች.ቲ.ኤም.ኤል. ግን ታዋቂው ነው። በድህረ ገጾች ላይ ጽሁፎች እና ምስሎች ይገኛሉ። እነዚህ ጽሁፎችና ምስሎች ወደ ሌላ ድህረ ገጽ ሊያገናኙ ይችላሉ።
በድህረ ገጽ ውስጥ የሚከተሉት ሊገኙ ይችላሉ፦
- ጽሁፍ
- ምስል
- ድምጽ
- መልታይ-ሚዲያ
- አፕሌት
ድህረ ገጾች ውስጥ የሚከተሉት ሊገኙ ይችላሉ ግን አይታዩም፦
- ስክሪፕቶች
- ሜታ ታግ
- ካስካዲንግ ስታይል ሺት
- አስተያየቶች
በአንድ ዌብ ሰርቨር ላይ የሚገኙ የተሰባሰቡ ድህረ ገጾች ዌብሳይት ይባላሉ። ዌብሳይቶች አብዛኛው ጊዜ index የሚባል የማውጫ ገጽ አላቸው። የአንድ ዌብሳይት አድራሻ ብቻ ሲጻፍ(ምሳሌ፦ www.wikipedia.org) ይህ የማውጫ ገጽ ይላካል።
[ለማስተካከል] ድህረ ገጾችን ማየት
ድህረ ገጾችን ለማየት ብዙ መንገዶች ሲኖሩ ድረገጽ ቃኚ ግን ዋነኛው ነው።
[ለማስተካከል] ድህረ ገጾችን መፍጠር
ድህረ ገጾችን ለመፍጠር አንድ ጽሁፍ መጻፊያ ሶፍትዌር ወይም ድህረ ገጽ መጻፊያ ሶፍትዌር ያስፈልጋል።