Web - Amazon

We provide Linux to the World


We support WINRAR [What is this] - [Download .exe file(s) for Windows]

CLASSICISTRANIERI HOME PAGE - YOUTUBE CHANNEL
SITEMAP
Audiobooks by Valerio Di Stefano: Single Download - Complete Download [TAR] [WIM] [ZIP] [RAR] - Alphabetical Download  [TAR] [WIM] [ZIP] [RAR] - Download Instructions

Make a donation: IBAN: IT36M0708677020000000008016 - BIC/SWIFT:  ICRAITRRU60 - VALERIO DI STEFANO or
Privacy Policy Cookie Policy Terms and Conditions
Wikipedia - እስልምና

እስልምና

From Wikipedia

እስልምና (ኢስላም) ማለት ነብዩ ሙሐመድ (የአላህ እዝነት እና ሰላም ይስፈንባቸው እና) ያስተማሩት ሃይማኖት የሚታወቅበት መጠሪያ ስም ሲሆን የእምነቱ ተከታዮች ደግሞ ሙስሊም በመባል ይታወቃሉ:: ኢስላም የሚለው ጥሬ ቃል ቋንቋ 3 ትርጉሞችን ያዘለ ሆኖ እናገኘዋለን:: እነሱም

1ኛ ከግልጽ ወይም ስወር ከሆኑ ጉድለቶች ፍጹም ነጻ የመሆን እና የመጥራት
2ኛ እርቅ እና እርጋታ
3ኛ ሰሚነት እና ቅን ታዛዥነት የሚለውን ትርጉም አዝሎ ይገኛል

[ለማስተካከል] የኢስላም ህጋዊ ትርጉም

ኢስላም ማለት የአላህን አንድነት (ተውሂድ) ማለትም በብቸኝነት አምልኮት ሁሉ ፍጹም ለእሱ ብቻ ሊሆን የሚገባው አምላክ ማለት ነው:: በመመሪያው በማደር ለትእዛዞቹ መንበርከክ : እመነትን እና ልቦናን ለአላህ ፍጹም ማድረግ እና ከአላህ ዘንድ የመጡ መመሪያዎችን በፍጹምነት ማመን ነው::

  • አንድ ሰው ሙስሊም ነው ሊባል የሚቻለው የዚህ ግዙፍ አለም ሆነ ሌላ አለ የሚባለው አለም እና በውስጧ ያሉት ነገሮች ሁሉ ፈጣሪ ተቆጣጣሪ አስተናባሪ ብቸኛ አምላክ አላህ ነው ብሎ ማመን እና

ነብዩ ሙሃመድ (ሰ.አ.ወ) የመጨረሻው መላክተኛ ናቸው ብሎ ማመን ነው:: ይህም በአጭር አማርኛ :- በእውነት የሚያመልኩት አምላክ ከአላህ በስተቀር የለም :: ነብዩ ሙሐመድም ባሪያው እና መላክተኛው ናቸው ብሎ ማመን ነው:: ይህም በአረብኛ «ላኢላሃ-ኢለሏህ ሙሃመድ ረሱሉሏህ» በመባል ይታወቃል:: ኢስላም እጅግ በጣም ቀላል እና ውስብስብስ ያልሆኑ መሰረታዊ የእምነት መርሆዎችን ያዘለ በመሆኑ እና ከሰው ልጅ መሰረታዊ እና ተፈጥሯዊ ፍላጎት ጋር የሚመጣተን ህግ እና ደንብ ያዘለ በመሆኑ እነሆ በዓለም ላይ ተከታዮቹ ከ1.2 ቢሊዮን በላይ ሆነው ይገኛሉ::

  • ኢስላም ለመረዳትም ሆነ ለማስረዳት እጅግ ቀላል ነው :: ከሌሎች እምነቶችም ልዩ የሚያደርገው የዚህን ዓለም ፈጣሪ አንድ ብቻ መሆኑን እና ሊመለክም የሚገባው ዕሱ ብቻ መሆኑን ማስተማሩ ሲሆን ለእርሱ ረዳትም ሆነ የስልጣን ተካፋይ ፈጽሞ የሌለው የሚፈልገውን ሰሪ ብቻውን ቀሪ ሃይል ጌታ አላህ ነው ብሎ ማመን ነው:: ከነብዩ ሙሃመድ ጀምሮ ሌሎች ነብያቶችም ሆኑ ታላላቅ መላእክት እንደ ጅብሪል ያሉትም እንክዋ ቢሆን የፈለጉትን የማድረግ ምንም አይነት ስልጣን የሌላቸው እና ለአላህ ፍጹም ታዛዥ መሆናቸውን ኢስላም ያስተምራል:: ስለዚህ ሙስሊሞች ነብዩ ሙሃመድንም ሆነ ሌሎችን ነብያቶች ከፈጣሪ መልእክት አድራሽ ናቸው ከማለት ውጭ በፍጹም በፍጹም አያመልኳአቸውም::
  • በዚህም መሰረት ነው በኢስላም እጅግ በጣም ታላቅ ወንጀል ማለት ከአላህ ሌላ ያሉ አክላታን ማምለክ ወይም ከአላህ ጋር ሌሎችም አካላት አብረው የስልጣን ተካፋይ ናቸው ብሎ ለነሱ ማጎብደድ አላህ ይቅር የማይለው ወንጀል ነው:: በይወት ዘመኑ በዚህ ወንጀል ተጸጽቶ እና ንስሃ ገብቶ እስካልተመለሰ ድረስ ከአላህ ሌላ ያለውን አካል እያመለክ የሞተ ሰው ገሃነም የዘለአለም መኖሪያው እንደሆነች እና ለሱም ምንም አይነት ረዳት እንደሌለው ኢስላም ጠንክሮ ያስተምራል:: እናም በአንድ ሃገር ሁለት መንግስት እንደማይኖር ሁሉ ይህ ዩኒቨረስም አንድ ፈጣሪ ብቻ ነው ያለው በማለት ኢስላም ሌሎች እንደ ፈጣሪ ተደርገው እንዳይመለኩ ያስጠነቅቃል:: ምክንያቱም ምን ነገር ማድረግ አቅሙም ሆነ ብልሃቱ የላቸውም እና ነው::

ኢማን (የልብ ስራ) 6 መሰረታዊ ነግሮችን አተቃልሎ ይዟል::

1ኛ በአላህ ማመን
2ኛ መላእክት እንዳሉት ማመን
3ኛ በኪታቡ (በመጽሃፎች ማመን)
4ኛ በሩሱሎች ማመን
5ኛ በመጨረሻው ቀን_የፍርድ ቀን (ሞቶ መነሳት) እንዳለ ማመን
6ኛ በቀደር ማመንን

የሚሉት ሲሆኑ ሰፋ ያለ ትንታኔ የሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ናቸው የኢስላም መሰረታዊ ነገሮች 5 ሲሆኑ

1ኛ አላህ አንድ ነው ሙሀመድ መላክተኛ ነው ብሎ ማመን
2ኛ ሰላት መስገድ
3ኝ ዘካ ማውጣት
4ና ጾም መጾም
5ኛ ሃጅ ማድረግ ናቸው
Our "Network":

Project Gutenberg
https://gutenberg.classicistranieri.com

Encyclopaedia Britannica 1911
https://encyclopaediabritannica.classicistranieri.com

Librivox Audiobooks
https://librivox.classicistranieri.com

Linux Distributions
https://old.classicistranieri.com

Magnatune (MP3 Music)
https://magnatune.classicistranieri.com

Static Wikipedia (June 2008)
https://wikipedia.classicistranieri.com

Static Wikipedia (March 2008)
https://wikipedia2007.classicistranieri.com/mar2008/

Static Wikipedia (2007)
https://wikipedia2007.classicistranieri.com

Static Wikipedia (2006)
https://wikipedia2006.classicistranieri.com

Liber Liber
https://liberliber.classicistranieri.com

ZIM Files for Kiwix
https://zim.classicistranieri.com


Other Websites:

Bach - Goldberg Variations
https://www.goldbergvariations.org

Lazarillo de Tormes
https://www.lazarillodetormes.org

Madame Bovary
https://www.madamebovary.org

Il Fu Mattia Pascal
https://www.mattiapascal.it

The Voice in the Desert
https://www.thevoiceinthedesert.org

Confessione d'un amore fascista
https://www.amorefascista.it

Malinverno
https://www.malinverno.org

Debito formativo
https://www.debitoformativo.it

Adina Spire
https://www.adinaspire.com