አክሱም
From Wikipedia
አክሱም በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ ክ/ሃገር ከአድዋ ተራራዎች አጠገብ የምትገኝ ከተማ ነች። በክርስቶስ ልደት አካባቢ ተመስርቶ የነበረው የአክሱም ስርወ መንግስት ማእከል ነበረች። የአክሱም ስርወ መንግስት በ12ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አካባቢ እየተዳከመ ሲመጣ የማእከላዊው መንግስት ወደ ደቡብ ተንቀሳቀሰ። ሰባአምስት በመቶ የሚሆነው የከተማው ነዋሪ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች ናቸው። የተቀሩት ነዋሪዎች የሱኒ እስልምና ተከታዮች ናቸው። ባላቸው ታሪካዊ ተፈላጊነት ከተማ ውስት የሚገኙት የአክሱም ስርወ መንግስት ቅሪቶች UNESCO በ1980 የአለም ቅርስ ቦታ ተብለው ተሰይሙአል።
አክሱም በኢትዮጵያ የ ትግራይ ክልል ከተማ ሲሆን በማዕከላዊ ዞንና በላዕላይ ማይጨው ወረዳ ይገኛል። በ1998 ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን እንደተመነው የ47,320 ሰው መኖሪያ ሲሆን ከነሱም 23,542 ወንዶችና 23,778 ሴቶች ይገኙበታል።[1]
በሌላ ገለልተኛ ትምና ደግሞ የ41,197 ሰው መኖሪያ ተደርጎ ተገምቷል። የከተማው አቀማመጥ በ14°07′ ሰሜን ኬክሮስ እና 38°44′ ምሥራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው።[2]
[ለማስተካከል] ምንጮች
- ↑ ማዕከላዊ የስታትስቲክስ ባለስልጣን, population.pdf
- ↑ Butler, Rhett A., 2005 population estimates for cities in Ethiopia
መደቦች: የኢትዮጵያ ከተሞች | ትግራይ | መዋቅሮች